ሀገሬ ቲቪ

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) ከአካባቢ አገራት ብሔራዊ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት ጋር ያለውን አጋርነት ለማጠናከር እንደሚሰራ የተቋሙ ዋና ፀሃፊ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ተናገሩ።

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) ከአካባቢ አገራት ብሔራዊ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት ጋር ያለውን አጋርነት ለማጠናከር እንደሚሰራ የተቋሙ ዋና ፀሃፊ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ተናገሩ።

የኢጋድ ዋና ፀሃፊው የመገናኛ ብዙኃን ሃሳቦችን በመግራትና ወደ አንድ መስመር እንዲተሙ በማድረግ ተጽዕኗቸው ከፍተኛ በመሆኑ የመገናኛ ብዙሃን የአንድን ማኅበረሰብ፣ ሕዝብ አልያም ደግሞ አገር መፃኢ እድል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በመወሰን የራሳቸው አስተዋጽዖ እንዳላቸው ጠቁመዋል።

በአካባቢው የሚገኙ በርካታ ሕዝቦች አሁንም ራዲዮን፣ ቴሌቪዥንና ጋዜጣን እንደ ዋና የመረጃ ምንጭነት የሚጠቀሟቸው የመገናኛ ብዙኃን መሆናቸውንም አንስተዋል።

ይህንንም ተከትሎ በአባል አገራቱ የሚገኙ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት በአካባቢው የሰላምና መረጋጋት፣ መልካም አስተዳደር እንዲሁም ዘላቂ ልማት ለማምጣት ሲሰሩ መቆየታቸውን ገልጸዋል።

እነዚህ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት በቀጣይም ይህንን አዎንታዊ አበርክቷቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀው ኢጋድም ከተቋማቱ ጋር ያለውን አጋርነት አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

በብሩክታዊት አስራት
2023-05-10