የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ በኢትዮጵያ የአሜሪካን ኤምባሲ ጉዳይ ፈፃሚ ከሆኑት አምባሳደር ትሬሲ ጃኮብሰን ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።
ሁለቱም በቆይታቸው ኢትዮጵያና አሜሪካን በሁለትዮሽ፣ በቀጣናዊና በባለብዙ ወገን ያላቸውን ትብብር ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ሀሳብ ተለዋውጠዋል።
አምባሳደር ጃኮብሰን በሱዳን የተፈጠረውን ቀውስ ተከትሎ አሜሪካን ዜጎቿን ለማስወጣት ባደረገችው ጥረት ላይ ኢትዮጵያ ላሳየችው ትብብር ምስጋና አቅርበዋል።
በብሩክታዊት አስራት
2023-05-16
