ሃንጋሪ ከአውሮፓ ህብረት ለዩክሬይን መድረስ የነበረባቸው 544 ሚሊየን ዶላር የሚያወጡ የጦር መሳሪያዎችን ማገዷ ተሰማ።
መሳሪያው ከአውሮፓ ህብረት በአውሮፓ የሰላም ተቋም በኩል ለኪየቭ የሚላክ እንደነበር አር ቲ ዎርልድ በዘገባው አስታውሷል።
ሃንጋሪ መሳሪያው ዩክሬይንን ለማስታጠቅ ብቻ የሚውል ከሆነ በእኔ በኩል አያልፍም ለዚህም ዋስትና ይሰጠኝ ስትል ጠይቃለች።
የሃንጋሪው ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክቶር ኦርባን አሜሪካ መራሹ የምዕራባውያን ጎራ ለዩክሬይን በቡዳፔስት በኩል ምንም አይነት የጦር መሳሪያ ማሳለፍ እንደማይችል ገልፀዋል።
የአውሮፓ የሰላም ተቋም መሰል የመሳሪያ አቅርቦት ለዩክሬይን ሲልክ ይህኛው ለ8ኛ ዙር ነበር ተብሏል፡፡
በአብርሃም በለጠ
2023-05-16
