ሀገሬ ቲቪ

ጭማሪ ያሳየው የባንኮች ተቀማጭ

የብሄራዊ ባንክ የተቀማጭ መጠን በሁለተኛው ሩብ ዓመት 21 በመቶ ጨመረ። ባንኮች ከሚሰበስቡት የተጣራ ቁጠባ በብሄራዊ ባንክ በመጠባበቂያ የሚያስቀምጡትን መጠን በእጥፍ እንዲያሳድጉ በመመሪያ መታዘዛቸው ይታወሳል። ያንንም ተከትሎ ከነሃሴ 26 አንስቶ ለሦስት ወር የማሟያ ጊዜ በማስቀመጥ ባንኮች የመጠባበቂያ ክምችታቸውን ከ 5 በመቶ ወደ 10 በመቶ እንዲያሳድግ ተወስኗል።

በውሳኔው መሰረት የባንኮች የመጠባበቂያ ክምችታቸው በበጀት ዓመቱ ሁለተኛ ሩብ መጨረሻ ከ 21 በመቶ በላይ መድረሱን ብሄራዊ ባንክ አስታውቋል።

የባንኮች የመጠባበቂያ መጠን አምና በተመሳሳይ ወቅት ከነበረውም ሆነ ከበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ አንፃር ከነበረበት 129 ቢሊየን ብር ወደ 145.1 ቢሊየን ብር ከፍ ብሏል።

በፍሬህይወት ታደሰ
2022-05-11