የአፍሪካ አንድነት ድርጅት (የአሁኑ የአፍሪካ ሕብረት) የተመሰረተበት 60ኛ ዓመት እና የአፍሪካ ቀን ዛሬ ይከበራል።
በየዓመቱ የአፍሪካ ቀን መከበር የጀመረው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት (አፍሪካ ህብረት) እ.አ.አ በ1963 መመስረቱን ተከትሎ ነው።
"የአፍሪካ ቀን" የአፍሪካዊያንን መራራ የነፃነት ትግልና ብሩህ ተስፋ በማሰብ የሚከበር ሲሆን፤ አፍሪካውያን ባህላቸውን፣ ትውፊታቸውን እና ስልጣኔያቸውን ለመላው ዓለም የሚያስተዋውቁበት በዓል ነው።
ቀኑ በአፍሪካ ሕብረት አዳራሽ በተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚከበር ሕብረቱ በድረ ገጹ ላይ ባሰፈረው መረጃ አስታውቋል።
የአፍሪካ ሕብረት የተመሰረተበትን 50ኛ ዓመት በምናከብርበት በዚህ ወቅት “የምንፈልጋትን አፍሪካ” እውን ማድረግ የምንችለው አጀንዳ 2063 ተግባራዊ በማድረግ መሆኑን አስታውቋል።
እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2013 ሕብረቱ ከተመሰረተ 50ኛ ዓመቱን ሲያስቆጥር፤ በቀጣይ 50 ዓመታት አህጉሪቷን በምጣኔ ሃብት፣ በፖለቲካና በማህበራዊ እድገት የተሻለ ደረጃ ላይ እንድትደርስ በማለም የ2063 አጀንዳ ተቀርፆ ወደ ትግበራ ተገብቷል።
በወንድማገኝ አበበ
2023-05-25
