ሀገሬ ቲቪ

የቴክኒክና ሙያ ዘርፉን በማበልፀግ ያለውን እምቅ አቅም ለሀገር ኢኮኖሚ እድገት መጠቀም ይገባል ሲሉ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ተናገሩ።

የቴክኒክና ሙያ ዘርፉን በማበልፀግ ያለውን እምቅ አቅም ለሀገር ኢኮኖሚ እድገት መጠቀም ይገባል ሲሉ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ተናገሩ።

በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አዘጋጅነት "ክህሎት ለተወዳዳሪነት" በሚል መሪ ሃሳብ 3ኛውን ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር ከተጀመረ አራተኛ ቀኑ ላይ ደርሷል።

ሚኒስትሯ በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ችግር ፈቺ የሆኑና የተለያዩ የፈጠራ ስራዎች አሉ፤ ዘፉን በተገቢው መንገድ በማበልፀግና በማሳደግ ያለውን እምቅ አቅም በመጠቀም የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ማሳደግ ይገባል ብለዋል።

የፓናል ውይይቱ ክህሎትን ለማበልፀግ፣ ለማልማት፣ ለመጠቀም የባለድርሻ አካላት ቅንጅትና ሚና፣ አዲሱ የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ ለቴክኒክና ሙያ ስልጠና እና ለስራ እድል ፈጠራ ያለው ሚና እና የክህሎት ውድድር ለስልጠና ጥራትና ለስራ እድል ፈጠራ ያለውን ጉልህ ሚና ላይ ያተኮረ ነው ተብሏል።

3ኛው አገር አቀፍ የክህሎት ውድድር ግንቦት 14 በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ መከፈቱ ይታወሳል።

በማህሌት አማረ
2023-05-25