የባህርዳር ደጋፊዎች ላይ በደረሰው የቦንብ ጥቃት 20 ሰዎች መጎዳታቸው ተነገረ፡፡
ይህ አደጋ የተፈጠረው ቡድናቸውን ለመደገፍ ሌሊት 10 ሰዓት ላይ በሙላለም የባህል ማዕከል አየተሰባሰቡ ባሉበት አጋጣሚ መሆኑ ታውቋል፡፡
በእግር ኳስ አፍቃሪያን ዘንድ በጉጉት የሚጠበቀው የቅዱስ ጊዮርጊስና የባህርዳር ከተማ ሊካሄድ 36 ሰዓት በቀረበት ወቅት በደጋፊዎቹ ላይ የደረሰው ጥቃት አነጋጋሪ ሆኗል።
ደጋፊዎቹ ቡድናቸውን ለመደገፍ ከባህርዳር ዩኒቨርስቲ የተፈቀደላቸውን አውቶቢስና ሌላ በተከራዩት ተጨማሪ አውቶቢስ ወደ አዲስ አበባ ለመምጣት በስንድት ላይ ነበሩ፡፡
በጉዳቱ እስካሁን የሞተ ሰው የሌለ ሲሆን ከ20 የሚበልጡ ደጋፊዎች ግን ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውን የአይን ምስክሮች ተናግረዋል።
ቦንቡ ተወርውሮ ይሁን ተጠምዶ በሚለውና አጠቃላይ ጉዳት ዙሪያ የክልሉ መንግስትና ፖሊስ የሚሰጠው መግለጫ እንደሚጠበቅ ሀትሪክ ስፖርት ዘግቧል።
በይገደብ ዓባይ
2023-05-25
