የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የ2015 ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር አጠቃላይ አሸናፊ ሆኗል።
ክህሎት ለተወዳዳሪነት በሚል መሪ ሀሳብ ከግንቦት 14/2015 ዓ.ም ጀምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት በአዲስ አበባ ሲካሄድ የነበረው የ2015 ሀገር አቀፍ የክህሎት ውድድር ተጠታቅቋል፡፡
ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ደረጃ በመውጣት ያሸነፉ ተወዳዳሪዎች ከ100 ሺህ እስከ 60 ሺህ ብር ድረስ የማበረታቻ ሽልማት፣ ዋንጫ፣ ሜዳሊያ እና የእውቅና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት 12 ወርቅ፣ 4 ብር እና 3 ነሃስ በማግኘት በአጠቃላይ ውጤት አንደኛ በመውጣት የ2015 ክህሎት ውድድር አጠቃላይ አሸናፊ ሆኗል።
የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት 9 ወርቅ፣ 10 ብር እና 7 ነሀስ በማግኘት በአጠቃላይ ውጤት ሁለተኛ ደረጃን ሲይዝ፤ አዲስ አበባ ከተማ ደግሞ 7 ወርቅ፣ 8 ብር እና 3 ነሀስ በማግኘት ሦስተኛ ደረጃን በማግኘት ውድድሩን አጠናቋል።
በብሩክታዊት አስራት
2023-05-27
