ሀገሬ ቲቪ

ዘመን ባንክ በ1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ ያስገነባው ባለ 36 ወለል የዋና መስሪያ ቤት ህንፃን አስመርቋል።

ዘመን ባንክ በ1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ ያስገነባው ባለ 36 ወለል የዋና መስሪያ ቤት ህንፃን አስመርቋል።

ህንፃው የከተማዋን ገጽታ ከማስዋቡ በተጨማሪ የኪነ-ህንፃ ውበት ጎልቶ የታየበት ነው ተብሏል።

እስከ 5ኛ ወለል ድረስ ከ200 በላይ መኪና ማቆሚያ እንዳለው ተነግሯል፡፡

ህንፃው ወደ ስራ መግባቱ ባንኩ ለዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ኪራይ በዓመት ከ40 ሚሊዮን ብር በላይ ሲያወጣ የነበረውን ወጪ የሚያስቀር መሆኑ ተገልጿል።

በ2 ሺህ 300 ካሬ ሜትር ስፋት ላይ ያረፈው ህንፃው የስብሰባ አዳራሾች፣ የአካል ብቃት ማጎልበቻ ክፍሎች፣ 6 አሳንሰሮች፣ 200 መኪና የሚይዙ የተሽከርካሪ ማቆሚያዎችና ሌሎች ክፍሎች አሉት ተብሏል፡፡

በናርዶስ ታምራት
2023-05-27