ሀገሬ ቲቪ

በኅብረት ሥራ ማህበራት ከ26 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን ተደራሽ ማድረግ ተችሏል ተባለ።

በኅብረት ሥራ ማህበራት ከ26 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን ተደራሽ ማድረግ ተችሏል ተባለ።

በግብርና፣ በቤቶች ልማት፣ በሸመታ፣ በመሰረተ ልማት እና በማዕድን ዘርፎች የኅብረት ስራ ማህበራትን በማደራጀት እየተሠራ መሆኑን በኢትዮጵያ የህብረት ስራ ኮሚሽን ማስፋፊያ እና አደረጃጀት ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ድሪባ በቀለ ተናግረዋል።

በዘርፋም ከ26 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን ተደራሽ ማድረግ መቻሉ ተጠቁሟል፡፡

የህብረተሰቡን ገቢ በማሳደግ፣ ኑሮ በማሻሻል፣ ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን በማጎልበት እና ቁጠባን ከማጠናከር አንፃር የማኅበራቱ ጠቀሜታው የጎላ ነው መባሉን ከኮሚሽኑ ማኅበራዊ ገፅ ተመልክተናል።

በሙሉጌታ በላይ
2023-05-30