የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተደራራቢ ግብርን ለማስቀረት እና በታክስ ላይ የሚፈፀመውን ማጭበርበር ለመከላከል የቀረበውን አዋጅ አፅድቋል፡፡
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 23ኛ መደበኛ ስብሰባውን በማካሄድ ላይ ይገኛል።
ምክር ቤቱ በኢትዮጵያ እና በግራንድ ዱቺ ኦፍ ሉዘምበርግ መካከል በገቢ ላይ የሚከፈለውን ግብር በሚመለከት በቀረበ ረቂቅ አዋጅ ዙሪያ መክሯል፡፡
በሀገራቱ መካከል ተደራራቢ ግብርን ለማስቀረት እና በታክስ ላይ የሚፈፀምን ማጭበርበር ለመከላከል የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ አስመልክቶ የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ አዋጁን አፅድቋል፡፡
በብሩክታዊት አስራት
2023-05-30
