ሀገሬ ቲቪ

የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባ ተጀምሯል፡፡

የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባ ተጀምሯል፡፡

የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን ማካሄድ ጀመረ።

ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ውይይቱን የጀመረው በቅርቡ በአሳዛኝ ሁኔታ ህይወታቸውን ላጡት ለፓርቲው ስራ አስፈፃሚ አባል አቶ ግርማ የሺጥላ የህሊና ፀሎት በማድረግ ነው።

ኮሚቴው በሚኖረው ቆይታ በሀገራዊ እንዲሁም በፓርቲያዊ ጉዳዮች ላይ ጥልቅ ውይይት በማካሄድ ውሳኔዎችንና ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል።

ለውይይት በተዘጋጁ ሠነዶች ላይ የጋራ ግምገማ በማድረግም መላውን ሕዝብ በማሳተፍ የሚሳኩ የብልፅግና ጉዞ ትልሞች ላይ እንደሚመክር ከፓርቲው ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በአብርሃም በለጠ
2023-05-30