ሀገሬ ቲቪ

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ዱግዳ ወረዳ አርሶ አደሮች፣ የቲማቲምና የአትክልት ማሳቸውን ወደ በጋ መስኖ ስንዴ እንዲቀይሩ መገደዳቸውን ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ዱግዳ ወረዳ አርሶ አደሮች፣ የቲማቲምና የአትክልት ማሳቸውን ወደ በጋ መስኖ ስንዴ እንዲቀይሩ መገደዳቸውን ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

በዚህም ሳቢያ የአትክልትና ፍራፍሬ አቅርቦት ችግር በመኖሩ የዋጋ መናር መከሰቱን ገልፀው፣ በቅርቡ የቲማቲም ዋጋ ጣሪያ የነካው ያልተጠበቀ ዝናብ እንዳለ ሆኖ የበጋ ስንዴ መዝራት ግዴታ ስለተደረገብን ነው ብለዋል።

በዱግዳ ወረዳ መቂ ዙሪያ አትክልትና ፍራፍሬ ማምረት ተከልክሎ እንደነበር የገለጹት አርሶ አደሩ፣ ተክለው የተገኙትም እንደተነቀለባቸውና የታሰሩም ጭምር መኖራቸውን ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

እንደ አርሶ አደሮቹ ገለጻ፣ በወረዳው ለስንዴና ለሌሎች ምርቶች እኩል ትኩረት ቢሰጣቸው የዋጋ መናሩ አይከሰትም ነበር ባይ ናቸው፡፡

የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ በበኩሉ የአመለካከት ችግር ተፈጥሮ ካልሆነ በስተቀር ስንዴ በሌሎች ምርቶች ላይ ተፅዕኖ አላሳደረም የሚል ምላሽ ሰጥቷል።

በብሩክታዊት አስራት
2023-05-31