በቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን መከስከስ ሕይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቤተሰቦች አውሮፕላኑ መሬት ላይ ከመከስከሱ አስቀድሞ ተጓዦቹ ለደረሰባቸው ሕመም እና ሰቀቀን ካሳ ሊጠይቁ ይችላሉ ተባለ።
Br>
ይህንን ያሉት በአሜሪካ ኤሊኖይስ ዳኛ የሆኑት ጆርጅ አሎንሶ ናቸው።
Br>
ከአራት ዓመታት በፊት የተከሰከሰው እና የኢትዮጵያ ንብረት የነብረው አውሮፕላኑ የ157 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ የአውሮፕላን አምራቹ ቦይንግ ተጓዦች ላይ የደረሰውን ህመም እና ሰቀቀን ከግምት ውስጥ አላስገባም ነበር ተብሏል።
Br>
ዳኛው አውሮፕላኑ ላይ በተፈጠረው አደጋ በጉዳት እና ሰቀቀን ተጓዦች ለመሞታቸው አንዱ ምክንያት ሊሆን ይችላል ብለዋል።
Br>
በአብርሃም በለጠ
2023-05-31
