ሀገሬ ቲቪ

ሱዳን አዲሱ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሀገሪቱ ተወካይን ውክልና አፅድቃለች።

ሱዳን አዲሱ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሀገሪቱ ተወካይን ውክልና አፅድቃለች።

በሱዳን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ልዩ መልዕክተኛ ሆነው የተመረጡት ቮልከር ፐርቴስ ተመድን የሚያስተባብረውን የሀገሪቱ የሽግግር ተልዕኮን እንደሚመሩም ነው የተገለፀው።

የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው የቮልከር ፐርቴስን የተመድን ልዩ መልዕክተኝነት መቀበሉን በመግለጫው አስታውቋል።

ፐርቴስ በአዲስ አበባ የተለያዩ ዲፕሎማሲያዊ ውይይት ያደረጉ ሲሆን ከ2021 ጀምሮ የሱዳን ጉዳይ ሲመሩ ቆይተውል።

በአብርሃም በለጠ
2023-06-09