የኢትዮጵያ አየር መንገድ በፈረንጆቹ 2035 የአውሮፕላኖቹን ብዛት 271 ለማድረስ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ፡፡
አሁን ላይ ወደ 140 በሚጠጉ አውሮፕላኖች እየተሰራ መሆኑን ተነግሯል፡፡
ከሰኔ 5 ቀን ጀምሮ አየር መንገዱ ከሚያዛቸው 29 አውሮፕላኖች ማለትም 17 የ737 ማክስ፣ አምስት 777ኤፍ ኤስ፣ አንድ 787-9 እና ሥድስት ኤርባስ ኤ350-1000 አውሮፕላኖች ይገኙበታል ተብሏል፡፡
በአፍሪካ 63 ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች ያሉት አየር መንገዱ፥ በአሁኑ ወቅት ያለውን 20 አውሮፕላን ማረፊያዎች ወደ 27 እንደሚያሳድግም ነው የተጠቆመው፡፡
በብሩክታዊት አስራት
2023-06-09
