ዩናይትድ ስቴትስ ለኢትዮጵያ ተጨማሪ 112 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገባች።
ዩኤስ ይህን ድጋፍ ለማድረግ ቃል የገባችው በ2030 ኢትዮጵያ ኤች አይቪ ኤድስን ለማስወገድ የምታደርገውን ተግባር ለመደገፍ መሆኑ ተሰምቷል፡፡
የአሜሪካ የአለም አቀፍ የኤድስ አስተባባሪ እና የጤና ዲፕሎማሲ ልዩ ተወካይ አምባሳደር ዶ/ር ጆን ንከንጋሶንግ ሀገራት በሰባት ዓመታት ውስጥ ኤች አይቪ ኤድስን ለማጥፋት የተሰናዳው COP23 የተሰኘው እቅድ መፅደቁን አስታውቀዋል።
የእቅዱ መፅደቅ ኢትዮጵያ በ2030 ወረርሽኙን የመከላከል ግብ ላይ ለመድረስ የሚያስችል ስራን ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር በትብብር ለመስራት ያስችላል ተብሏል።
በባለፉት 20 ዓመታት ለዚሁ ተግባር 3 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ድጋፍ መደረጉ ይታወሳል፡፡
በአብርሃም በለጠ
2023-06-09
