የዓለማችን ቱጃር ኤለን መስክ ዶናልድ ትራምፕን ወደ ትዊተር እመልሰዋለሁ አለ። ባለሀብቱ ትዊተር የቀድሞ የአሜሪካን ፕሬዝዳንት ለማገድ የወሰነው ውሳኔ ስህተት እና ሞኝነት ነው ሲሉ ገልጸውታል። በ 44 ቢሊዮን ዶላር ትዊተርን የግሉ ያደረገው መስክ ትዊተር ሀሳብን በነጻነት መግለጫ መድረክ እንደመሆኑ ብዙም አልተሰራበትም ማለታቸው ይታወሳል። ታዲያ ኤለን መስክ ከዚህ ገጽ የታገዱትን የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን እንደገና ወደ ገጹ አመጣቸዋለሁ ሲሉ ለፋይናንሺያል ታይምስ ተናግረዋል።
በዮ
2022-05-11
