ሀገሬ ቲቪ

ህብረተሰቡ እራሱን ከአጭበርባሪዎች መጠበቅ እንዳለበት ተጠቆመ፡፡

ህብረተሰቡ እራሱን ከአጭበርባሪዎች መጠበቅ እንዳለበት ተጠቆመ፡፡

አንዳንድ ግለሰቦች እና ድርጅቶች የግብርና እና የሪል ስቴት ኢንቨስትመንት ላይ መሰማራታቸውን በመግለፅ ከህብረተሰቡ ገንዘብ እንደሚሰበስቡ አገልግሎቱ መረጃ እንደደረሰው የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ገልጿል።

ቅንጡ የመኖሪያ አፓርትመንቶችን በዝቅተኛ ዋጋ እንደሚሸጡ እና የአክሲዮን በመግዛት በአጭር ጊዜ ውስጥ ትርፋቸውን በእጥፍ ማሳደግ እንደሚችሉ በተለያዩ መንገዶች እያስተዋወቁ ናቸው ብሏል።

ስለሆነም ህብረተሰቡ ከመሰል ድርጊቶች ጋር ተያይዞ ሊፈፀም ከሚችል መጭበርበር እራሱን እንዲጠብቅ እና የጥንቃቄ እርምጃም እንዲወስድ አገልግሎቱ አሳስቧል።

በማህሌት አማረ
2023-06-14