የአሜሪካን ብሔራዊ ሚስጥራዊ ሰነዶች አግባብ ባልሆነ አያያዝ ጋር በተያያዘ ክስ ተመስርቶባቸው ፍርድ ቤት የቀረቡት የቀድሞ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጥፋተኛ አይደለሁም ሲሉ ተከራክረዋል።
ትራምፕ ከፍርድ ቤት ውሏቸው በኋላ ወደ ኒው ጀርዚ በማቅናት ለደጋፊዎቻቸው ንግግር አድርገዋል።
ትራምፕ ግን የክሱ መጨረሻ ምንም ይሁን ምን ቀጣዩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆኖ ለመመረጥ የሚያደርጉትን ትንቅንቅ እንደማያቆሙ ለደጋፊዎቻቸው ቃል ገብተዋል።
ሕግ ባለሙያዎች ትራምፕ በቀረቡባቸው ክሶች ጥፋተኛ የሚባሉ ከሆነ እስር ሊጠብቃቸው ይችላል ብለዋል።
በናርዶስ ታምራት
2023-06-14
