ለዓባይ ግድብ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡ ተነገረ፡፡
በበጀት ዓመቱ አስር ወራት ለዓባይ ግድብ ግንባታ ከአንድ ቢሊዮን 188 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን የግድቡ ብሔራዊ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡
ግድቡ ከተጀመረ ጊዜ ጀምሮ እስከ ሚያዝያ ወር መጨረሻ የተሰበሰበው ጠቅላላ ገንዘብ ከ17 ቢሊዮን 971 ሚሊዮን ብር በላይ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
ገቢው የተሰበሰበው ከአገር ውስጥና ከውጭ አገራት ቦንድ ሽያጭ፣ ከ8100 አጭር የጽሑፍ መልዕክት እና ከልዩ ልዩ ገቢዎች መሆኑን ና ከአገር ውስጥ ቦንድ ሽያጭና ስጦታ ከ920 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡ ተነግሯል፡፡
ከዲያስፖራ ቦንድ ሸያጭና ስጦታ ከ35 ሚሊዮን ብር በላይ እንዲሁም በኢትዮጵያ ኤሌትሪክ ኃይል የስጦታ አካውንት ከ111 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተገኝቷልም ተብሏል፡፡
በተጨማሪም ከአጭር የሞባይል መልዕክት አገልግሎት በ8100 ከ122 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡ ተጠቅሷል፡፡
የተሰበሰበው ጠቅላላ ገቢ ከአገር ውስጥ ቦንድ ሽያጭና ስጦታ ከ15 ነጥብ ሰባት ቢሊዮን ብር በላይ፣ ከዲያስፖራ ቦንድ ሽያጭና ስጦታ አንድ ነጥብ አራት ቢሊዮን ብር በላይ እና ከልዩ ልዩ ገቢዎች ከ777 ሚሊዮን ብር በላይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በብሩክታዊት አስራት
2023-06-17
