የመቀሌ ኢንዱስትሪ ፓርክ በቅርቡ ወደ ሥራ እንደሚገባ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አስታወቀ፡፡
ፓርኩ ውስጥ መዋዕለ ንዋያቸውን ያፈሰሱ ባለሀብቶችም ተመልሰው ሥራቸውን እንዲቀጥሉ የሚያስችሉ ውይይቶች መደረጋቸው ተጠቅሷል፡፡
በተደረገው የዳሰሳ ጥናት በፓርኩም ሆነ በባለሀብቶች ንብረት ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት ባለመድረሱ ፓርኩን ወደ ሥራ ለመመለስና ባለሀብቶችም በቀላሉ ተመልሰው ሥራቸውን እንዲቀጥሉ ለማድረግ ትልቅ አቅም የሚፈጥር መሆኑ ተመላክቷል፡፡
የፓርኩ ወደ ሥራ መመለስ የሥራ ዕድል በመፍጠር፣ የውጭ ምንዛሪ በማስገኘት፣ የእውቀት ሽግግር ለማድረግና አካባቢው ላይ ተፈጥሮ በነበረው አለመረጋጋት ያጋጠመውን የኢኮኖሚ መዳከም ለማነቃቃት ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረክታልም ነው የተባለው፡፡
በአብርሃም በለጠ
2023-06-17
