ሀገሬ ቲቪ

5 የውጭ አገር ባንኮች ኢትዮጵያ ውስጥ ገብተው አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችላቸው ፈቃድ እንደሚሰጣቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ፡፡

5 የውጭ አገር ባንኮች ኢትዮጵያ ውስጥ ገብተው አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችላቸው ፈቃድ እንደሚሰጣቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የገንዘብ ተቋማት ዘርፍ ምክትል ገዥ አቶ ሠለሞን ደስታ የአገር ውስጥ የፋይናንስ ተቋማትን ከማጠናከር ጎን ለጎንም የውጭ ባንኮችን ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት እየተሰራ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

‹‹ሥራውን አሁን እያጠናቀቅን ነው፤ አዋጁን የመከለስ ሥራውንም እያጠናቀቅን ነው፤ ከለጋሾች አንዳንድ ግብዓቶችን እየጠየቅን ነው፤ በወራት ዕድሜ ለህዝብ እንደራሴዎች ይቀርባል፤ ስለዚህ ስራው እየተፋጠነ ነው” ብለዋል አቶ ሠለሞን::

በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ከሦስት እስከ አምስት ለሚደርሱ የውጭ ባንኮች ፈቃድ ለመስጠት እቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑንም አቶ ሠለሞን ገልጸዋል፡፡

የውጭ ባንኮች የአገር ውስጥ ባንኮችን ከገበያ እንዳያስወጧቸው የአገር ውስጥ የፋይናንስ ተቋማት አቅም ግንባታ ላይ ሊሰሩ ይገባል፤ ለዚህም የተቀመጠ አሰራር መኖሩን አመልክተዋል፡፡

ከውጭ ከሚመጡ ተቋማትም ጋር እንዴት በቅንጅት መስራት እንዳለባቸው ከወዲሁ ማሰብ ይጠበቅባቸዋል፤ ካፒታል፣ እውቀት እና ቴክኖሎጂ እንዴት መጋራት እንደሚቻልም ባንኮቹ ከወዲሁ ሊያጤኑት ይገባል ሲሉም አክለዋል፡፡

በብሩክታዊት አስራት
2023-06-22