ሀገሬ ቲቪ

በኢትዮጵያ የፈረንሳይ ኤምባሲ ለኢትዮጵያ ሚዲያ የድጋፍ ፕሮግራም በዛሬው ዕለት አስጀምሯል።

በኢትዮጵያ የፈረንሳይ ኤምባሲ ለኢትዮጵያ ሚዲያ የድጋፍ ፕሮግራም በዛሬው ዕለት አስጀምሯል።

በኢትዮጵያ የፈረንሳይ ኤምባሲ አምባሳደር ረሚ ማሪሾ እንደገለጹት፤ የፈረንሳይ ኤምባሲ በዚህ አዲስ የኢትዮጵያ ሚዲያ ድጋፍ ፕሮግራም የ944 ሺህ ዩሮ ወይም የ57 ሚሊዮን ብር በጀት መድቧል።

በቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት የሚቆየው ይህ ፕሮግራም ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ምክር ቤት እና ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ጋር በመሆን የሚሰራ ይሆናል ብለዋል።

በተጨማሪም ሁለት የፈረሳይ ድርጅቶች ካናል ፍራንስ ኢንተናሽናል (CFI) እና የኦዲዮቪዥዋል ብሔራዊ ተቋም (INA) የኢትዮጵያ ሚዲያን ለማገዝ በአጋርነት ይሰራሉ ተብሏል።

በማህሌት አማረ
2023-06-22