ሀገሬ ቲቪ

የ60 ሺህ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ማስጀመሪያ ስነ-ስርዓት ተካሂዷል፡፡

የ60 ሺህ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ማስጀመሪያ ስነ-ስርዓት ተካሂዷል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመንግሥት እና የግል አጋርነት መርሃ ግብር የ60 ሺህ መኖርያ ቤቶች ቅድመ ማስጀመሪያ ስነ-ስርዓት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተገኙበት ተካሄዷል፡፡

ቤቶቹ በ5 ዓመታት ጊዜ ውስጥ ተገንብተው የሚጠናቀቁ ሲሆን ከ250 ሺህ በላይ ለሚሆኑ የከተማ ወጣቶች ቀጥተኛ የስራ ዕድል የሚፈጠርላቸው ይሆናል፡፡

በመኖሪያ ቤት ግንባታ ለመሰማራት ፍላጎት ካሳዩ 70 የግል ድርጅቶች ውስጥ ኦቪድ ግሩፕ ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቅቆ በቅድመ ማስጀመሪያ ስነ-ስርዐት ላይ ተገኝቷል፡፡

60 ሺህ ቤቶችን በ5 ዓመታት ውስጥ ገንብቶ ለተጠቃሚዎች እንደሚያስተላልፍም የከንቲባ ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡

በሙሉጌታ በላይ
2023-06-22