ሀገሬ ቲቪ

በደብረ ብርሃን ከተማ የተገነባው የበላይነህ ክንዴ ቢዝነስ ግሩፕ ፌቤላ የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካ ወደ ማምረት ሥራ መሸጋገሩ ተገልጿል።

በደብረ ብርሃን ከተማ የተገነባው የበላይነህ ክንዴ ቢዝነስ ግሩፕ ፌቤላ የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካ ወደ ማምረት ሥራ መሸጋገሩ ተገልጿል። ፋብሪካው በኤሌክትሪክ የሚሰሩ ሚኒባስ፣ ሚዲባስ እና የከተማ አውቶብስ ተሽከርካሪዎችን ማምረት መጀመሩ ነው የተነገረው፡፡ ፋብሪካው እስካሁን ለ150 ዜጎች ቋሚ፣ ለ100 ዜጎች ጊዜያዊ የሥራ እድል ተጠቃሚ መድረጉ ተገልጿል፡፡ በሙሉ አቅሙ ወደ ሥራ ሲገባም ለ440 ዜጎች ቋሚ፣ ለ250 ለሚሆኑ ዜጎች ጊዜያዊ በአጠቃላይ ከ700 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ እድል እንደሚፈጥር ተነግሯል፡፡ ፋብሪካው በመጀመሪያ ዙር 216 መኪኖችን ለመገጣጠም አቅዶ እየሰራ መሆኑንና ከ20 ቀን በኋላ የሚገጣጥማቸውን በኤሌክትሪክና በነዳጅ የሚሰሩ መኪናዎች ለገበያ ማቅረብ እንደሚጀምር ተነግሯል፡፡ ፋብሪካው በቀን 4 በነዳጅና በኤሌክትሪክ የሚሰሩ መኪኖችን መገጣጠም እንዲሚችልና፤ ጥሬ እቃውን ለጊዜው ከቻይና እና ከአውሮፓ በማምጣት እንደሚገጣጠሙም ተሰምቷል፡፡ የኤሌክትሪክ መገጣጠሚያ ፋብሪካው 2 ቢሊየን ብር ወጪ ተደርጎበታልም ተብሏል፡፡

በናርዶስ ታምራት
2023-06-22