ሀገሬ ቲቪ

በቤተሙከራ የተሰራ ስጋ በአሜሪካ ለገበያ እንዲቀርብ ፈቃድ አገኘ::

በቤተሙከራ የተሰራ ስጋ በአሜሪካ ለገበያ እንዲቀርብ ፈቃድ አገኘ::

ኦፕሳይድ ፉድስ እና ጉድ ሚት የተባሉ ሁለት የአሜሪካ ኩባያዎች በቤተሙከራ የተሰራ ስጋን እንዲሸጡ በትናንትናው ዕለት ከአሜሪካ ግብርና ሚኒስቴር ፈቀድ ማግኘታቸውን አልዐይን ዘግቧል።

ለሁለቱ ኩባንያዎች የተሰጠው ፈቃድም በሀገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በቤተሙከራ የተሰራ ስጋ የምርት ሽያጭ መንገድ መክፈቱን ሮይተርስ አስነብቧል።

ድርጅቶቹ ከእንስሳት ህዋሶች ናሙና የተገኘ በመጠቀም በቤተ ሙከራ ውስጥ የተሰራው ምርት “ስጋ” ተብሎ እንዲመዘገብ ባለብዙ ደረጃ የማፅደቅ ሂደት በማጠናቀቅ ቀዳሚ ናቸው ተብሏል።

አሜሪካ በቤተ ሙከራ ለተሰራው ስጋ ፈቃድ መስጠቷን ተከትሎ በላብራቶሪ የተመረተ ስጋን በመሸጥ ከሲንጋፖር በመቀጠል ሁለተኛዋ ሀገር ሆናለች።

በሳይንሳዊ ሂደት የሚመረተው ስጋ ጤናማነትም በአሜሪካ የምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ተረጋግጦ የሰው ልጆች ይመገቡት ዘንድ ቀደም ብሎ ፈቃድ መስጠቱ ይታወሳል።

በማህሌት አማረ
2023-06-22