በሚቀጥሉት 5 ዓመታት ለሚተገበረው የተቀናጀ የአካባቢ ጥበቃና ልማት ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል የ9.3 ሚሊዮን ዶላር ፕሮጀክት ተፈርሟል፡፡
ፕሮጀክቱ የአየር ንብረት አካታች ተቋማዊ የአቅም ግንባታ፣ ከአየር ንብረት ጋር የሚጣጣም ቴክኖሎጂ ተደራሽነት፣ የተቀናጀ የመሬት አያያዝ እና የገቢ ምንጭ አማራጮችን ማስፋትን የሚመለከቱ አራት ዘርፎች ያሉት መሆኑም ተመላክቷል፡፡
ፕሮጀክቱ በተመረጡ ክልሎችና ወረዳዎች ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑም ከገንዘብ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
ለፕሮጀክቱ ማስፈፀሚያ ከተመደበው ገንዘብ ውስጥ 8.9 ሚሊዮን ዶላር የሚሆነው ግሎባል ኢንቫይሮመንት ፋሲሊቲ ከሚባል አለም አቀፍ ተቋም እንዲሁም 400 ሺህ የአሜሪካ ዶላሩ ደግሞ ከተባባሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም መሆኑ ታውቋል፡፡
የፋይናንስ ድጋፍ ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሰመሪታ ሰዋሰው፣ የኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳሬክተር ዶክተር ጌታሁን ጋረደው፣ የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም የኢትዮጵያ ተወካይ ሚስተር ቱርሃን ሳሌህ ፈርመውታል፡፡
በወንድማገኝ አበበ
2023-06-22
