ኦሮሚያ ገቢዎች ቢሮ ከኢትዮ ቴሌ ኮም ጋር ግብርን በቴሌ ብር ለመሰብሰብ የሚያስችለውን ስምምነት ፈፅሟል፡፡
ስምምነቱን የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ እና በምክትል ኘሬዝዳንት ማዕረግ የኦሮሚያ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ መስከረም ደበበ ተፈራርመዋል፡፡
በ2010 ዓ.ም 16 ቢሊየን ብር የተሰበሰበ ሲሆን በ2015 ዓ.ም 71 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር መሰብሰቡን የኦሮሚያ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ መስከረም ደበበ ተናግረዋል፡፡
በ2016 ዓ.ም 130 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ መታቀዱን ጠቅሰው የታክስ አሰባሰብ ሥርዓቱን ዘመናዊና ምቹ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የኢትዮ ቴሌ ኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ በበኩላቸው በኢትዮ ቴሌኮም ቴሌ ብር ተግባራዊ ከተደረገ ጊዜ ጀምሮ 34 ሚሊየን ደንበኞችን አፍርቷል ብለዋል፡፡
በናርዶስ ታምራት
2023-06-22
