ሀገሬ ቲቪ

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የሰብዓዊ ተቋማት ጥምረት በይፋ ተመስርቷል።

የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የሰብዓዊ ተቋማት ጥምረት በይፋ ተመስርቷል።

የኢጋድ የሰላም እና ደህንነት ዘርፍ ጥምረቱን ለመመስረት ላለፉት ሶስት ቀናት በኬንያ ሞምባሳ ሲያካሂድ የነበረው አውደ ጥናት ዛሬ አጠናቅቋል።

የሰብዓዊ ተቋማት ጥምረቱ በኢጋድ ቀጣና ዴሞክራሲ እና መልካም አስተዳደር ለማስፈን እንዲሁም ለመጠበቅ እየተከናወኑ ላሉ የጋራ ጥረቶች ወሳኝ ምዕራፍ መሆኑን በዝግጅቱ ላይ የታደሙት ዶክተር ወርቅነህ ገልጸዋል።

ከጥምረቱ ምስረታ በተጨማሪ የጥምረቱ ማቋቋሚያ እና የስራ ኃላፊነት ረቂቅ የሕግ ማዕቀፍ ፀድቋል።

የኢጋድ አባል አገራት አውደ ጥናቱን አስመልክቶ የጋራ መግለጫ ያወጡ ሲሆን በሕግ ማዕቀፉ ላይም ፊርማቸውን አኑረዋል።

በሙሉጌታ በላይ
2023-06-24