ሀገሬ ቲቪ

የቻይናው ዋይ ቲ ኦ ኩባንያ በሞጆ ከተማ የትራክተር ማምረቻ ፋብሪካ ሊገነባ ነው።

የቻይናው ዋይ ቲ ኦ ኩባንያ በሞጆ ከተማ የትራክተር ማምረቻ ፋብሪካ ሊገነባ ነው። .

ኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ በዓመት 10 ሺህ ትራክተሮችን ማምረት የሚያስችል ፋብሪካ ለመገንባት ከቻይናው ዋይ ቲ ኦ ኩባንያ ጋር ተፈራርሟል፡፡ .

ፋብሪካው በሞጆ ከተማ የሚገነባ ሲሆን ተገንብቶ ሲጠናቀቅ በቀን 50 እና በዓመት ከ10 ሺህ በላይ ትራክተሮችን የማምረት አቅም ያለው መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡ .

ፕሮጀክቱ ኢትዮጵያ በዘርፉ የምታወጣውን የውጪ ምንዛሪ በማስቀረትና የውጪ ምንዛሪን በማስገኘት ረገድ ከፍተኛ ፋይዳ እንደሚያበረክት ተገልጿል፡፡ .

በአብርሃም በለጠ
2023-06-24