ሀገሬ ቲቪ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በፓሪስ ላደረጉላቸው አቀባበል እና ሽኝት ምስጋና አቅርበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በፓሪስ ላደረጉላቸው አቀባበል እና ሽኝት ምስጋና አቅርበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት መልዕክት “የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በፓሪስ ላደረጉልን አቀባበል እና ሽኝት ምስጋናዬን አቀርባለሁ” ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም “ፍሬያማ ለነበረው አዲስ የዓለም አቀፍ የፋይናንስ ስምምነት ጉባዔ እንዲሁም የአፍሪካ ሀገሮችን ለመደገፍ ላሳዩት ፈቃደኛነትም አመሰግናቸዋለሁ” ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በናርዶስ ታምራት
2023-06-24