የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የንብረት ግብር አካል በሆነው ተሻሽሎ በቀረበው የቤት ግብር ብቻ በዓመት እስከ 6 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ ገቢ እንደሚያገኝ ታሳቢ መደረጉ ተገለጸ፡፡
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ አቶ ኑር አደም እንደገለጹት፣ በተሻሻለው የቤት ግብር አዲስ ተመን መሠረት በከተማው ውስጥ ካሉ ግብሩ ከሚመለከታቸው ቤቶች በዓመት ከ5 እስከ 6 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ ገቢ የከተማው አስተዳደር ያገኛል ተብሎ ታሳቢ ተደርጓል፡፡
እስካሁን ድረስ የከተማ አስተዳደሩ ከቤት ግብር ሲሰበሰብ የነበረው 47 ሚሊዮን ብር እንደሆነ ያስታወሱት አቶ አደም፤ ይህም አስተዳደሩ ከሚሰበስበው ጠቅላላ ግብር ውስጥ ከቤት ግብር የሚሰበሰበው 0.08 በመቶ ብቻ ድርሻ ያለው መሆኑን ያሳያል ብለዋል፡፡
ግብሩ የሚሰበሰበው ከ ከ891 ሺህ በላይ ከሚሆኑ ቤቶች ነው፡፡
በከተማው ውስጥ 1.02 ሚሊዮን ቤቶች ይኖራሉ ተብሎ እንደሚታመን እና የቀበሌና የመንግሥት ቤቶች የቤት ግብር እንደማይማይመለከታቸው መነገሩን ሪፖርተር ዘግቧል።
በወጋየሁ አንዳርጌ
2023-06-26
