ሰሜን ኮሪያ የኮሪያ ጦርነት ዓመታዊ ክብረ በዓልን ምክንያት በማድረግ አሜሪካን ለማውገዝ ሰልፍ አካሂዳለች።
በፒዮንግያንግ 73ኛ ዓመት የኮሪያ ጦርነት የፈነዳበትን አሜሪካን ለመደምሰስ "የበቀል ጦርነት" የሚል መፈክሮችን በማሰማት ህዝባዊ ስብሰባዎችን አካሂዳለች።
በመዲናዋ በተካሄደው ሰልፎች ላይ 120,000 የሚጠጉ ሰራተኞች እና ተማሪዎች መሳተፋቸውን የመንግስት የዜና ወኪል ኬሲኤንኤ ዘግቧል።
መላው የአሜሪካ መዲና በኛ የተኩስ ክልል ውስጥ ነው የሚሉና ሌሎች መፈክሮችን ይዘው ታይተዋል፡፡
የኑክሌር ጦር መሳሪያ የታጠቀችው ሰሜን ኮሪያ ትልቁን አህጉር አቋራጭ የባልስቲክ ሚሳዬል ጨምሮ የተለያዩ መሳሪያዎችን ስትሞክር ከደቡብ ኮሪያ እና ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር ያለውን ውጥረት እያጋጋለችው መሆኑ ተነግሯል፡፡
በብሩክታዊት አስራት
2023-06-26
