ሀገሬ ቲቪ

የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ወታደራዊ ኃይል በዋና ከተማው ካርቱም የሚገኘውን ከፍተኛ የፖሊስ ማዘዣ ጣቢያ መቆጣጠሩን አስታወቀ።

የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ወታደራዊ ኃይል በዋና ከተማው ካርቱም የሚገኘውን ከፍተኛ የፖሊስ ማዘዣ ጣቢያ መቆጣጠሩን አስታወቀ።

ወታደራዊ ኃይሉ ባወጣው መግለጫ በደቡብ ካርቱም የሚገኘውን ትልቁን የፖሊስ ማዘዣ ሰፈር ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሪያለሁ ብሏል።

በማዘዣ ጣቢያው 160 የጭነት መኪናዎችን፣ 75 የጦር መሣሪያ እና 27 ታንኮችን ማግኘቱን አስታውቋል።

የሱዳን ጦር በበኩሉ የግለሰብ ተሽከርካሪዎችን ለጦርነት እየተጠቀመ ነው ሲል ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉን ከስሷል።

በሱዳን መከላኪያ እና በሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል የሚደረገው ወጊያ 11ኛ ሳምንቱን አስቆጥሯል።

ጦርነቱ በካርቱም፣ በባህሪ እና በኦምዱርማን በሚገኙ ሦስት ከተሞች ውስጥ ተፋፍሟል ቀጥሏል።

በወንድማገኝ አበበ
2023-06-26