ሀገሬ ቲቪ

ተቃወሞ የገጠመው የታሊባን ህግ

ታሊባን የሀግሪቱ ሴቶች ሰውነታቸውን እና ፊታቸውን ይሸፍኑ ሲል ያወጣውን አዲስ ህግ በርካታ የአፍጋኒስታን ሴቶች ለመቃወም አደባባይ ወጥተዋል። ህጉ ሰውነታቸን ከመሸፈን በተጨማሪ የሀገሪቱ ሴቶች አስፈላጊ ጉዳይ ከሌላቸው ከቤት እንዳይወጡ የሚከለከል ነው። ይህን የ ታሊባን ህግ ያልተከተለች ማንኛውም ሴት የመንግስት ሰራተኛ ከስራ የምትባረር ሲሆን ወንዶችም የትዳር አጋሮቻቸውን ባለመጠበቅ ቅጣት ይተላለፍባቸዋል ተብሏል። ታዲያ ይሄን ህግ ለመቃወም በርካታ ሴቶች አደባባይ ቢወጡም በ ሀገሪቱ የጸጥታ ሀይል እንዲበተኑ ተደርጓል ሲል ኤፒ ዘግቧል።

በዮሴፍ ከበደ
2022-05-11