ሀገሬ ቲቪ

መንግሥት 29 ሚሊዮን ሊትር ዘይት በብድር ሊገዛ መሆኑን አስታወቀ።

መንግሥት 29 ሚሊዮን ሊትር ዘይት በብድር ሊገዛ መሆኑን አስታወቀ።

የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅትና የገንዘብ ሚኒስቴር በትብብር 29 ሚሊዮን ሊትር ዘይት በብድር ለመግዛት መዘጋጀታቸው ተሰምቷል፡፡

የዘይቱ ጠቅላላ የመግዣ ዋጋ 43 ሚሊዮን ዶላር ብድር በገንዘብ ሚኒስቴር ዋስትና ከአንድ ዓመት በኋላ የሚከፈል መሆኑን የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት አስታውቋል።

እስከ ጥቅምት 2016 ዓ.ም. 29 ሚሊዮን ሊትር ዘይት ወደ አገር ውስጥ ይገባል ተብሎም ይጠበቃል፡፡

ግዥውን የሚፈጽመው ኢትዮ ብላክ የተሰኘ የአገር ውስጥ ኩባንያ መሆኑm ተገልጿል።

በወጋየሁ አንዳርጌ
2023-06-26