ኢትዮጵያ በህዳሴው ግድብ ድርድር ዙሪያ የአረብ ሊግ ጣልቃ ገብነትን እንደማትቀበል ም/ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ገለፁ።
የአረብ ሊግ ጣልቃ ገብነት ተገቢነት የሌለው ነው ሲሉም ተችተዋል።
ግብፅ፣ ሱዳን እና ኢትዮጵያ የግድቡን የውሃ ሙሌት በተመለከተ የሶስቱም ሀገራት ባለሙያዎችን የሚያስማማ ሰነድ ተዘጋጅቷል ያሉት አቶ ደመቀ የግብፅ እና የሱዳን ስጋትንም ለመፍታት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
በመጭው ሐምሌ እና በነሐሴ ወራትም የህዳሴ ግድብ አራተኛ ዙር ሙሌት እንደሚከናወን ተገልጿል።
በማህሌት አማረ
2023-06-26
