ሀገሬ ቲቪ

በዕርዳታዎች ላይ በሚፈፀሙ ስርቆቶች ምክንያት በኢትዮጵያ የሚደረገው የምግብ ዕርዳታ በመቆሙ አስፈሪ ሁኔታዎች መኖራቸውን የዩናይትድ ስቴትስ የሰብአዊ እርዳታ ኤጀንሲ (USAID) ገለፀ፡፡

በዕርዳታዎች ላይ በሚፈፀሙ ስርቆቶች ምክንያት በኢትዮጵያ የሚደረገው የምግብ ዕርዳታ በመቆሙ አስፈሪ ሁኔታዎች መኖራቸውን የዩናይትድ ስቴትስ የሰብአዊ እርዳታ ኤጀንሲ (USAID) ገለፀ፡፡

ባለፉት ሳምንታት አሜሪካ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የእርዳታ እህልን ወደ ኢትዮጵያ መስደድ ካቆሙ በኋላ በተለያዩ አካባቢዎች የረሃብ አደጋዎች መከሰታቸውን በዚህም ሳቢያ ሰዎች መሞታቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት ገልፀዋል።

የዕርዳታ ተቋማቱ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለስልጣናት በዕርዳታ ስርቆት ተሳታፊ መሆናቸውን የገለፁ ሲሆን በጉዳዩ ላይ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የዓለም የምግብ ፕሮግራም የተለየ ምርመራ ለማድረግ ከዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ጋር ተስማምተዋል።

በብሩክታዊት አስራት
2023-06-30