ሀገሬ ቲቪ

የሬሜዲያል ፕሮግራም ፈተናዎች መሰረዛቸውን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

የሬሜዲያል ፕሮግራም ፈተናዎች መሰረዛቸውን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

በትናንትናው እለት የተሰጡት ፈተናዎች ውድቅ ተደርገው ከዛሬ ጀምሮ በሚሰጡ ፈተናዎች እንዲፈተኑ ውሳኔ ማሳለፉንም ገልጿል።

በተጨማሪም ቀደም ብሎ በሁሉም ሬሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ ተማሪዎች ባላቸው ተቋማት ፈተናውን በአንድ ጊዜ ለመስጠት መታቀዱ ይታወቃል።

ይሄም ተሻሽሎ በተለይም ከ150 በላይ የሆኑና ከ200 በላይ ካምፓስ ያላቸውን የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፈተና ቀርቶ ወደ ፊት በሚወሰን አግባብ ፈተናው በመስከረም ወር 2016 ዓ.ም እንዲሰጥ አሳውቋል።

በመንግስት ተቋማት የሬሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ የሆኑትን ተማሪዎች በተያዘው ፕሮግራም መሰረት የሚሰጥ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

በማህሌት አማረ
2023-07-04