የኢትዮ-ካዛኪስታን የቢዝነስ ፎረም በአስታና ተካሄዷል።
በፎረሙ ላይ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ የተመራ ከፍተኛ ልዑካን ቡድን ተሳትፏል።
አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ በኢትዮጵያ ስላለው የኢንቨስትመንት አቅም እና ለውጭ ባለሃብቶች በመንግሥት በኩል ስለተሰጡ ማበረታቻዎች ገለጻ አድርገዋል።
በኢትዮጵያ የውጭ ኢንቨስትመንት በየጊዜው እያደገ መምጣቱንና ያሉ ምቹ ሁኔታዎችን በማየት የመዳረሻ አቅሞች እየሰፉ መምጣታቸውን በውይይቱ ወቅት ተገልጿል።
በፎረሙ ላይ ለካዛኪስታን የንግድ ድርጅቶች ተወካዮች በኢትዮጵያ ያሉ የኢንቨስትመንት አማራጮች እና እድሎች በተመለከተ ማብራሪያ ቀርቧል።
የካዛኪስታን ከፍተኛ የቢዝነስ ልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ ያለውን የኢንቨስትመንት አማራጮች ለመቃኘት የስራ ጉብኝት ያደርጋል ተብሎ እንደሚጠበቅም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
በብሩክታዊት አስራት
2023-07-05
