በአዲስ አበባ የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መሰጠት ተጀምሯል፡፡
የመልቀቂያ ፈተናው በ182 የፈተና ጣቢያዎች ነው እየተሰጠ ያለ ሲሆን 75 ሺህ 90 ተማሪዎች ለመውሰድ መመዝገባቸው መገለጹ ይታወቃል።
በየካ ክፍለ ከተማ የካራአሎ ቅድመ መጀመሪያና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 570 የመንግሥት፣ የግል እና የርቀት ትምህርት ተማሪዎች ለፈተና ተቀምጠዋል።
ፈተናውን የሚወስዱ ተማሪዎች በዕድሜ አነስተኛ በመሆናቸው ፈተናውን ሲወስዱ ያለምንም ጭንቀት ተረጋግተው ሰዓታቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙ መደረጉ ተነግሯል፡፡
በትምህርት ቤቱ በፈተና ወቅት ለሚያጋጥሙ የጤናም ሆነ ሌሎች ችግሮች የሕክምና ባለሙያ በመመደብ ቅድመ ዝግጅት መደረጉን ኢዜአ ዘግቧል።
በአብርሃም በለጠ
2023-07-05
