ሀገሬ ቲቪ

የኒውክሌር ማበልጸጓን ትቀጥላለች የተባለችው ሰሜን ኮሪያ

ሰሜን ኮሪያ የኒውክለር እና ሚሳኤል ፕሮግራሟን እንደምትቀጥል ተጠቆመ። 14 ያክል የሚሳኤል ሙከራዎችን በያዝነው የፈረንጆቹ 2022 ያደረገችው ሰሜን ኮሪያ አሁንም የመቀጠል እቅዶች እንዳሏት ተጠቁሟል። ይህንን የጠቆሙት ለሴኔት ባቀረቡት ገለጻ የአሜሪካ የመረጃ ተቋም ኃላፊዎች ናቸው። ሰሜን ኮሪያ የወታደራዊ አቅሟን ማጠንከሯን እና ባላስቲክ ሚሳኤል ማበልጸጓን የመቀጠል እቅድ አላት ተብሏል።

በሳምሶን ገድሉ
2022-05-11