ሀገሬ ቲቪ

የትምህርት ሚኒስቴር የመጽሃፍት ሥርጭትና ቁጥጥርን ለማቀላጠፍ የሚረዳ ትራክ ኤንድ ትሬስ የተሰኘ ዲጂታል መተገበሪያ ማዘጋጀቱን ይፋ አደረገ።

የትምህርት ሚኒስቴር የመጽሃፍት ሥርጭትና ቁጥጥርን ለማቀላጠፍ የሚረዳ ትራክ ኤንድ ትሬስ የተሰኘ ዲጂታል መተገበሪያ ማዘጋጀቱን ይፋ አደረገ።

መተግበሪያው ለተማሪዎች የመማሪያ መጽሃፍት አስተዳደር የሚያግዝ መሆኑም ተገልጿል።

በትምህርት ሚኒስቴር የአይሲቲ እና ዲጂታል ትምህርት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ዘላለም አሰፋ የዲጂታል መተግበሪያው የአገልግሎት ሽፋን ከመጽሃፍት አታሚ ድርጅቶች አንስቶ በተማሪዎች እጅ እስከሚደርስ ያለውን ሂደት እና የመጽሃፍት አገልግሎት ጊዜን ጭምር የሚያጠቃልል መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ የሚታተሙ የተማሪ መማሪያ መጽሃፍት እያንዳንዳቸው የየራሳቸው ባርኮድና QR ያላቸው ሆነው እንደሚታተሙም ተናግረዋል፡፡

የዲጂታል መተግበሪያው በሚገባው ልክ ውጤታማ እንዲሆንም በባለሙያዎች ዳብሮና ጸድቆ ወደ ሙከራ ትግበራ የገባ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡

በዚህም መሠረት ዲጂታል መተግበሪያው በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አምስት ትምህርት ቤቶችን መሠረት በማድረግ ወደ ሙከራ ትግበራ የገባ ሲሆን በ2016 ዓ.ም ሁሉንም የሀገሪቷን ትምህርት ቤቶች መሠረት በማድረግ በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ተግባራዊ እንዲሆን እየተሰራ እንደሚገኝ ትምህርት ሚኒስቴር በማህበራዊ ገፁ አስፍራል፡፡

በወንድማገኝ አበበ
2023-07-05