ሀገሬ ቲቪ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) የ2015 በጀት ዓመት በመንግሥት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ የሚሰጡትን ምላሽና ማብራሪያ ያዳምጣል፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) የ2015 በጀት ዓመት በመንግሥት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ የሚሰጡትን ምላሽና ማብራሪያ ያዳምጣል፡፡

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን 28ኛ መደበኛ ጉባዔውን ነገ ያካሂዳል።

ምክር ቤቱ ነገ በሚያካሂደው 28ኛ መደበኛ ስብሰባ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) የፌደራል መንግሥት የ2015 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ከምክር ቤት አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች የሚሰጡትን ምላሽና ማብራሪያ ያዳምጣል፡፡

ምክር ቤቱ በውሎው የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የ2016 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀትን አስመልክቶ የሚያቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሐሳብ መርምሮ የበጀት አዋጁን እንደሚያጸድቅም የጠበቃል።

በናርዶስ ታምራት
2023-07-05