በኢትዮጵያ ባንኮች በቁጠባ የሰበሰቡት ገንዘብ 2 ነጥብ 1 ትሪሊዮን ብር መድረሱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትናንትናው ዕለት የ2015 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ከምክር ቤት አባላት ለቀረበላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በፋይናንስ ዘርፉ ባለፉት አምስት ዓመታት አመቺ የሆኑ መመሪያዎችን ማውጣት፣ የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማትን ወደ ባንክ ማሳደግ፣ በዲጂታል ባንኪንግና በሌሎችም ተግባራት በመከናወናቸው እድገት መመዝገቡን አሳውቀዋል።
ከዚሁ ጋር በተገናኘ የባንኮች እና የቁጠባ ሂሳብ ደብተር ያላቸውን ሰዎች ቁጥር አድጓል እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለጻ።
ከአምስት ዓመት በፊት በቁጠባ የተሰበሰበው ሃብት ከ1 ትሪሊዮን ያነሰ እንደነበር አስታውሰው፤ በአሁኑ ወቅት 2 ነጥብ 1 ትሪሊዮን ደርሷል ነው ያሉት።
በወጋየሁ አንዳርጌ
2023-07-07
