የደቡብ አሜሪካ መሪዎች ዘሌንስኪ ስብሰባ ላይ እንዳይገኙ እገዳ ማድረጋቸው ተገለጸ፡፡
33 አባላት ያሉት የደቡብ አሜሪካ ህብረት በሐምሌ 17 ጀምሮ በብራስልስ ከአውሮፓ ህብረት ጋር የጋራ ስብሰባ ለማድረግ ታቅዷል።
በዚህ ስብሰባ ላይ ስፔን መጀመሪያ ላይ ዘሌንስኪን እንዲገኝ ብትጋብዝም የላቲን አሜሪካ እና የካሪቢያን ግዛቶች ማህበረሰብ (ሲኤላሲ) መሪዎች ተቃውሞ ምክንያት የዩክሬኑን ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዘሌንስኪ ከመጪው የጋራ ጉባዔ እንደማይገኙ ተገልጿል፡፡
ዩክሬን በጉባዔው ላይ እንዳትገኝ ያደረጋት ምክንያት የደቡቡብ አሜሪካ መሪዎች “በአውሮፓ ውስጥ ላለው ወቅታዊ ግጭት እና የዲፕሎማሲያዊ መሻከሮች ምክንያት የዩክሬን የሚደረገው ድጋፍ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
በናርዶስ ታምራት
2023-07-07
