ሀገሬ ቲቪ

የአፍሪካ ሕብረት የአፍሪካ ትስስር ቀንን በሕብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ እያከበረ ይገኛል።

የአፍሪካ ሕብረት የአፍሪካ ትስስር ቀንን በሕብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ እያከበረ ይገኛል።

ቀኑ እየተከበረ ያለው “በአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ገበያ የስራ ፈጠራ፣ የዲጂታል እና ፋይናንስ አካታችነትን ማፋጠን” በሚል መሪ ሀሳብ ነው።

በመርሐ-ግብሩ ላይ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀ-መንበር ሞኒክ ንሳንዛባንጋዋ፣ የአፍሪካ ሕብረት የንግድ ቱሪዝም፣ ኢንዱስትሪ እና ማዕድን ኮሚሽነር አልበርት ሙቻንጋ፣ የቀድሞ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ የስራ እና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል የአፍሪካ ቀጣናዊ ተቋማት አመራሮች እና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።

የቀኑን አከባበር አስመልክቶ በከፍተኛ ባለስልጣናት ደረጃ የተዘጋጁ የጎንዮሽ ውይይት እና ፓናል እንደሚካሄድ ተገልጿል።

የአፍሪካ ሕብረት በቀጣናው እና በአህጉራዊ ደረጃ እየተደረጉ ባሉ የትስስር ሂደቶች የተገኙ ቁልፍ ስኬቶችን ለማስታወስ እንዲሁም የተገኙ ትምህርቶችን መሰረት አድርጎ በትስስሩ የነበሩ እና አሁን እየታዩ ያሉ ፈተናዎች ምላሽ መስጠት በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ መምከር እንዲቻል የአፍሪካ ትስስር ቀን በየዓመቱ እ.አ.አ ሐምሌ 7 እንዲከበር ወስኗል።

በብሩክታዊት አስራት
2023-07-07