የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት በ2016 በጀት 140.29 ቢሊዮን ብር እንዲኾን አጽድቋል።
የጸደቀው በጀት ከአምናው ጋር ሲነጻጸር በ40.21 በመቶ ጭማሪ ያለው ሲሆን፤ በረቂቅ አዋጅ ለካፒታል በጀት ትኩረት በመስጠት 77.99 ቢሊዮን ብር ወይም አጠቃላይ ከጸደቀው በጀት 55.59 በመቶውን የሚይዝ ነው፡፡
ለካፒታል በጀት ትኩረት መስጠታችን የከተማዋን ዘላቂ እና መሰረታዊ ዕድገት ለማስቀጠል ሰፋፊ የሥራ እድል ለመፍጠር ታሳቢ ያደረገ ነው ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል።
በአብርሃም በለጠ
2023-07-10
