በቀጣዩ ዓመት ሁሉም የፋይናንስ ተቋማት ደንበኞቻቸውን ወደ ዲጂታል መታወቂያ እንዲያስገቡ ሊደረግ ነው ተባለ፡፡
ብሔራዊ ባንክ እና የኢትዮጵያ የዲጂታል መታወቂያ ፕሮጀክት ኹሉም የፋይናንስ ተቋማት በ2016 ዓ.ም ደንበኞቻቸውን ወደ ዲጂታል መታወቂያ እንዲያስገቡ የሚያስችል መርሃ ግብር መቅረጻቸውን ይፋ እድርገዋል።
የፋይናንስ ደኅንነትን ለማስጠበቅ "ደንበኛህን በኤሌክትሮኒክ ዘዴ እወቅ" የተሰኘ ሁለተኛ መርሃ ግብር ተግባራዊ እንደሚደረግም ተገልጧል።
ሁለተኛው መርሃ ግብር ማንኛውም ሰው በአካል መቅረብ ሳያስፈልገው የፋይናንስ ተቋማት በዲጂታል አማራጭ ብቻ ግለሰቡን ደንበኛ ለማድረግ የሚያስችላቸውና የገንዘብ ማጭበርበርን የሚቀንስ መርሃ ግብር ነው ተብሏል።
በብሩክታዊት አስራት
2023-07-11
